ኢጋድ ና ሱዳን   በሀገሪቱ የተፈጠረውን  ቀውስ በሚረግብበት ሁኔታ ላይ  ለመምክር ተስማሙ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 17/2016(ኢዜአ)፡- ኢጋድ ና ሱዳን   በሀገሪቱ የተፈጠረውን  ቀውስ በሚረግብበት ሁኔታ ላይ  ለመምክር ተስማሙ።

የሱዳን  ሉአላዊ የሽግግር መንግስት ሊቀመንበር   አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ  በሱዳን ቀውስ ላይ አስቸኳይ ምክክር ለማድረግ መስማማታቸውን  የሱዳን መንግስት  አስታወቀ፡፡

አል ቡርሃን በሀገሪቱ የተፈጠረውን ቀውስ  ለመፍታት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ  ከኢጋድ ሊቀመንበር  ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ለመምከር  ፍላጎታቸውን ያሳዩት  ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር  ጌሌ በተወያዩበት   ወቅት ነው፡፡

አልቡርሃን እና የኢጋድ ሊቀመንበር ምክክራቸውን በሳውዲ አረቢያ እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን የሱዳን ታጣቂ ሃይሎችና ፈጠኖ ደራሽ ሃይሉ በምክክሩ እንደሚገኙም የሱዳን መንግስት መግለጫ አመልክቷል፡፡

በመግለጫው  የኢጋድ አስቸኳይ ጉባኤ  የሱዳንን  አሁናዊ የግጭት ሁኔታ  እንዲፈታ ከሁሉም አካላት ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ቅዳሜ እለት ባወጣው መግለጫ በሱዳን ያለውን ግጭት አውግዞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሀገሪቱ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠየቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም