የግብርና ሚኒስትሩና የሲዳማ ክልል አመራሮች ችግኞችን ተንከባከቡ - ኢዜአ አማርኛ
የግብርና ሚኒስትሩና የሲዳማ ክልል አመራሮች ችግኞችን ተንከባከቡ
አዲስ አበባ ፤ኅዳር 16/ 2016/ (ኢዜአ)፦ የግብርና ሚኒስትሩና የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በአዋሳ የታቦር ተራራ ላይ የተተከሉ ችግኞችን ተንከባከቡ ፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት ለአረንጓዴ አሻራ የተጣለውን ግብ ለማሳካት በክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ጽድቀት በቅርበት መከታተልና መንከባከብ ይገባል ።
ማህበረሰቡም ሆነ ተቋማት በክረምት ወቅት የተከሏቸውን ችግኞች የመንከባከብና ውሃ የማጠጣት ስራ አጠናክረው መቀጠል ይኖርበቸዋል ነው ያሉት ።
ሚኒስትሩ በሲዳማ ክልል በሚኖራቸው ቆይታ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፕሮጀክት (LFSDP) ድጋፍ የተከናወኑና ሌሎች ልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ ከግብርና ሚኒስቴር ማህበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።