ቀጥታ፡

መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እየሰራች ነው

 አዲስ አበባ ፤ ህዳር 14/2016 (ኢዜአ) ፦ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት በተለያዩ የትብብር መስኮች ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ የአገሪቱ አምባሳደር ፈርናንድ ኮኖ ገለጹ።

አምባሳደር ፈርናንድ ኮኖ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው።

ሁለቱ አገራት ጠንካራ አጋርነት ያላቸው መሆኑን ጠቁመው በተለይም በንግድና በአቬይሽን ዘርፍ ያለውን የሁለቱ አገራት ግንኙነት ለአብነትም አንስተዋል።  

ይህም አጋርነት አህጉሪቱ ውህደት ለመፈጸም የምታደርገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል።  

በቀጣይም ሁለቱ አገራት ያላቸውን አጋርነት በተለያዩ የትብብር መስኮች ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ለዚህም በቅርቡ ሥምምነቶች እንደሚደረጉ ተናግረዋል።  

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው አፍሪካ ባንጊ ከተማ አቋርጦት የነበረውን የቀጥታ በረራ በቅርቡ ዳግም መጀመሩ ይታወሳል።  

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም