ኢንስቲቲዩቱ "የአፍሪካ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የልሕቀት ማዕከል” እንዲሆን የቀረበውን ሃሳብ የጋራ ኮሚቴው ተቀበለው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 13/2016(ኤዜአ)፦ የኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት "የአፍሪካ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የልሕቀት ማዕከል” እንዲሆን የጋራ የቴክኒክ ኮሚቴው ያቀረበውን ምክረሃሳብ የሚንስትሮች ምክርቤት የጋራ ኮሚቴ ተቀበለው።

የአፍሪካ የአይሲቲ እና ኮሚኒኬሽን ሚንስትሮች መደበኛ ጉባኤ በህብረቱ የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው ኢትዮጵያን በመወከል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር የኤሌክትሮኒክ መንግስት ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢንጂነር አብዮት ሲናሞ እየተሳተፉ ይገኛሉ።


 

በስብሰባው የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት “የአፍሪካ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የልሕቀት ማዕከል” እንዲሆን በኢትዮጵያ በኩል ጥያቄው ቀርቦ በአፍሪካ አገራት የአይሲቲና የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴሪያል አባላት ቀርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት በጋራ ኮሚቴው ተቀባይነት አግኝቷል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በኮሚኒኬሽን እና በአይሲቲ ላይ የሚመክረው የልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ከህዳር 10 እስከ 12 ቀን 2016 በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ ለሦስት ቀናት መካሄዱ እና ውሳኔዎች እንደቀረቡበት ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም