ቀጥታ፡

10ኛው ዙር አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት መርሃ-ግብር የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 13/2016 (ኢዜአ)፦  10ኛው ዙር አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት መርሃ-ግብር የፊታችን ቅዳሜ የሚካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ መብራቱ የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚሁ መርሃ-ግብር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዓለም አቀፍ የጥራት መስፈርትን ላሟሉ ተቋማት ሽልማት የሚበረከት መሆኑን ገልፀዋል።

ከመወዳደሪያ መስፈርቶቹ መካከል የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የኃብት አጠቃቀም፣ የአመራር ሰጪነት፣ የደንበኞች አያያዝ፣ የሥራ አፈጻጸምና ሌሎችንም ጨምሮ ሰባት መስፈርቶች መኖራቸውን ዘርዝረዋል።

ከተመረጡት ዘርፎች መካከል የጤና፣ የሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ፣ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ይገኙበታል ብለዋል፡፡

በዚሁ መሠረት 39 ድርጅቶች እስከ ውድድሩ መጨረሻ የዘለቁ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ተሸላሚዎቹ የፊታችን ቅዳሜ ይለያሉ ነው ያሉት።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም