ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ፖሊሲ ለማሻሻል ሁለተኛ ጥናት ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 13/2016 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ላለፉት አስር ዓመታት ሥራ ላይ የዋለውን የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ፖሊሲ ለማሻሻል ተጨማሪ ጥናት ሊያካሂድ ነው። 

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ፖሊሲ ለማሻሻል እየተከናወኑ ባሉ የጥናት ሥራዎች አስመልክቶ ዛሬ ውይይት ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ከጅማ፣ ከወሎ፣ ከሐዋሳና ከጅግጅጋ ዩኒቨርስቲዎች ጋር ጥናት ለማካሄድና የጥናቱን ውጤት ተከትሎ ፖሊሲውን ለማሻሻል በ2013 ዓ.ም የመግባቢያ ሥምምነት ፈጽሟል።    

ይህንንም ተከትሎ በጅማ ዩኒቨርስቲ አስተባባሪነት ለሁለት ዓመታት ሲካሄድ ከቆየው ጥናት በተጨማሪ   በወሎ ዩኒቨርስቲ አስተባባሪነት በነዚሁ ዩኒቨርስቲዎች ተጨማሪ ጥናት ለማካሄድ ዛሬ ሥምምነት ተደርጓል። 


 

ጥናቱ ለቀጣይ ስምንት ወራት የሚካሄድ ሲሆን የሁለቱ ጥናት ውጤቶች ከግምት በማስገባት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ፖሊሲ ማሻሻያ ሥራ እንደሚጀመር ነው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የገለጸው። 

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ፖሊሲውን  በመረጃና ጥናቶች ላይ ተመስርቶ ለማሻሻል እየተሰራ ነው።

የፖሊሲ ማሻሻያው ዳያስፖራው በአገር ቤት የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲያስችለው ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን ጠቁመዋል።  

ያም ብቻ ሳይሆን ዳያስፖራው ባላቸው የሙያ ስብጥርና አቅምን ከግምት በማስገባት ዘርፉን በአግባቡ ለመምራት በማለም ማሻሻያው እንደሚደረግም ነው ያብራሩት።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም