የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ60 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 13/2016 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ60 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል::

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በማብሰሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለክልሉ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከንቲባዋ ለክልሉ ማቋቋሚያ እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ የ60 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማበርከቱን መግለጻቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም