ዋሊያዎቹ በቡርኪና ፋሶ ተሸነፉ - ኢዜአ አማርኛ
ዋሊያዎቹ በቡርኪና ፋሶ ተሸነፉ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 11/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ 2ኛ የምድብ ጨዋታ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ያደረገው ጨዋታ በቡርኪና ፋሶ 3 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
የቡርኪናፋሶን የማሸነፊያ ግቦች ብላቲ ቱሬ በ69 ኛው፣ በርትራንድ ትራኦሬ (ፍ) በ78ኛው፣ ዳንጎ ኦታትራ 90ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡
ዋሊያዎቹ በቀጣይ የምድቡን ሶስተኛ እና አራተኛ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ከጊኒ ቢሳኦ እና ጅቡቲ ጋር እንደሚያደርጉም ታውቋል።