ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከቡርኪና ፋሶ አቻቸው ጋር ዛሬ ይጫወታሉ - ኢዜአ አማርኛ
ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከቡርኪና ፋሶ አቻቸው ጋር ዛሬ ይጫወታሉ
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 11/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ 2ኛ የምድብ ጨዋታ የቡርኪና ፋሶ አቻውን ዛሬ ከቀኑ በ10 ሰዓት ይገጥማል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቡርኪና ፋሶው ጨዋታ በካዛብላንካ ሞላይ ራሺድ ስታዲየም ልምምዱን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን ከዛሬ ጨዋታው በፊት የመጨረሻ ልምምዱን በትላንትናው ዕለት አድርጓል።
ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በኤል-አብዲ ስታዲየም ከቡርኪና ፋሶ ጋር ጨዋታውን እንደሚያደርግ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ጃሜህ ለሚን ከጋምቢያ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ሲመራ የሀገሩ ዜጎች ጃዎ አብዱልአዚዝ (ረዳት)፣ ዳርቦ ኦማር (ረዳት) እና ሳላህ ኦማር (አራተኛ) እንዲሁም አውዪ ዩሱፍ ከዩጋንዳ በኮሚሽነርነት ተመድበዋል።