ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የ'ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ' ጉባኤን ተካፈሉ

164

አዲስ አበበ ፤ ህዳር 10/2016 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ'ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ' ጉባኤን ተካፍለዋል::

በ2017 የጀርመን የጂ20 ፕሬዝዳንትነት ዘመን የተጀመረው የጂ20 'ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ' (CWA) ለውጥ ተኮር በሆኑ የአፍሪካ ሀገራት፣ በጂ 20 አጋሮች ብሎም ከእነዚህ ባሻገር ባሉ አካላት መካከል የንግግር እና የትብብር መድረክ ሆኗል::


 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢኮኖሚ ትብብር እና የግሉን ዘርፍ በማጠናከር በሚመለከተው ክፍለ ውይይት ላይ መሳተፋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም