በኢንጂነር አይሻ መሃመድ የተመራ ልዑክ በኮሪያ ሪፐብሊክ ጄዱ ራስ ገዝ አስተዳደር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን ሪጅን ዋና መስሪያ ቤትን ጎበኘ

67

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 10/2016 (ኢዜአ) ፦ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ የሚመራ ልዑክ በኮሪያ ሪፐብሊክ ጄዱ ራስ ገዝ አስተዳደር ማህበረሰብ ኮርፖሬሽን ሪጅን ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱም ጥናትና ዲዛይን እንዲሁም በኮርፖሬሽኑ ስለሚገነባው የሲየንግ አፕ የመስኖ ግድብ በተመለከተ በኮርፖሬሽኑ ዳይሬክተር ጀነራል ዶንግ ቺኦል እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ገለጻ ተደርጓል።

የሲየንግ አፕ የመስኖ ግድብ 1ነጥብ 25 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለውና 400 ሄክታር የሚያለማ መሆኑም ተመላክቷል።


 

በተመሳሳይም በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ የተመራ ቡድን የሲየንግ አፕ ግድብን በአካል ተገኝቶ ጎብኝቷል፡፡

ለልዑኩ በተደረገለት ገለፃ ልምድ ማግኘት መቻሉም ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም