በቀጣዩቹ ደረቅና ፀሃያማ ቀናት ቅንጅታዊ አሰራርን በመተግበር የደረሱ ሰብሎችን መሰብሰብ ይገባል -ግብርና ሚኒስቴር - ኢዜአ አማርኛ
በቀጣዩቹ ደረቅና ፀሃያማ ቀናት ቅንጅታዊ አሰራርን በመተግበር የደረሱ ሰብሎችን መሰብሰብ ይገባል -ግብርና ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፤ ህዳር 10/2016(ኢዜአ)፦ በቀጣዩቹ ደረቅና ፀሃያማ ቀናት ቅንጅታዊ አሰራርን በመተግበር የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት መሰብሰብ እንደሚገባ የግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
አርሶ አደሮች፣ አመራሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቅንጅታዊ አሰራርን በመተግበር የደረሱ ሰብሎችን በግዜ ሰብስበው በጥንቃቄ ወደ ጎተራ ማስገባት እንዳለባቸው አስረድቷል።
ግብርና ሚኒስቴር እንዳመለከተው የኢትዮጵያ ሜቲዮሮሎጂ ኢንስቲቲዮት የትንበያ መረጃ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ስለሚኖር ለመኸር ሰብል ምርት ተገቢውን ጥንቃቄ ካልተደረገ የምርት ብክነት ሊያስከትል እንደሚችል አስታውቋል፡፡