ጎንደር ከተማን ወደ ተሟላ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ ያለመ ውይይት መካሄድ ጀመረ

ጎንደር፤  ህዳር 10/2016 (ኢዜአ )- ጎንደር ከተማን ወደ ተሟላ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ ያለመ ውይይት መካሄድ ጀመረ ።

በከተማው ዛሬ የተጀመረው የውይይት መድረክ 'ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ጎንደርን እንገንባ'' በሚል መሪ ሃሳብ ላይ ያተኮረ ነው።

ውይይቱ በተለያዩ ቀበሌዎች በ95 መድረኮች እየተካሄደ ሲሆን ሴቶች፣ ወጣቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የንግዱ ማህበረሰብ እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

በከተማው ያለውን ሰላም ዘላቂ በማድረግ ጎንደርን ወደ ተሟላ ሰላምና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መሰረት ተደርጎ ውይይቱ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

መድረኩ በከተማው የተገኘውን  ሰላም ዘላቂ በማድረግ ህብረተሰቡ የጀመረውን የሰላም ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ አበበ ላቀው አስታውቀዋል።

የከተማውን ሰላም ዘላቂ በማድረግ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴን ማጠናከር እንዲቻል ህዝቡ የቀጣይ የሰላም ተልእኮውን ተገንዝቦ የድርሻውን እንዲወጣ ማስቻል የውይይቱ አላማ መሆኑን  አቶ አበበ ጨምረው አስታውቀዋል ።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም