ጃቪየር ሚሌ የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

107

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 10/2016 (ኢዜአ) ፦ በአርጀንቲና የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጃቪየር ሚሌ ተቀናቃኛቸውን ሰርጂዮ ማሳን በመብለጥ የአገሪቱን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ አሸነፉ፡፡

ተቀናቃኛቸው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሰርጂዮ ማሳ ውጤቱን በጸጋ እንደሚቀበሉና ተመራጩን ፕሬዚደንት እንኳን ደስ ያሉት ለማለት አንደሚያገኟቸው ተናግረዋል፡፡

90 በመቶ ያህሉ የመራጮች ድምጽ ተቆጥሮ በተገኘ ጊዜያዊ ውጤት ሚሌ ከአምሳ አምስት በመቶ በላይ ድምጽ ሲያገኙ ተቀናቃኛቸው ሰርጂዮ ደግሞ 44 በመቶ ማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡

በዚህም ለቀጣይ አራት አመታት የላቲን አሜሪካዊቷን አገር አርጀንቲናን ለመምራት መመረጣቸውን ነው የቢቢሲ ዘገባ የሚያሳየው።

ከውጤቱ በኋላ የምርጫው አሸናፊ ሚሌ በዋና ከተማዋ ቦነስ አይረስ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ዛሬ አርጀንቲና እንደገና የምትገነባበት፣ ከውድቀት የምትነሳበት ልዩ ቀን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም