በጀርመን ከመራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ጋር በሀገሮቻችን መካከል ያለውን የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር የበለጠ ለማጠናከር የሁለትዮሽ ውይይት አድርጊያለሁ-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

163

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 9/2016 (ኢዜአ) ፦ በጀርመን ከመራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ጋር በሀገሮቻችን መካከል ያለውን የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር የበለጠ ለማጠናከር የሁለትዮሽ ውይይት አድርጊያለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በንፁህ ኃይል፣ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት፣ በማዳበሪያ ምርት ብሎም በቀጣናዊ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ትብብራችንን ለማጠናከር ተስማምተናል ብለዋል።

ኢትዮዽያ እና ጀርመን በአየር ጠባይ ለውጥ፣ በኃይል ምንጭ፣ በትምህርት፣ በቀጣናዊ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች የጠበቀ ትብብር አላቸው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም