ቀጥታ፡

በአዲስ አበባ የሰራናቸው ስራዎች ወደ ሌሎች የሃገራችን አካባቢዎች መስፋፋት ተቀናጅቶና ተናብቦ መስራትን ያጠናክራሉ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 9/2016 (ኢዜአ) ፦ የሁላችን ቤት በሆነችው አዲስ አበባ የሰራናቸው ስራዎች ወደ ሌሎች የሃገራችን አካባቢዎች መስፋፋት ተቀናጅቶና ተናብቦ መስራትን ያጠናክራሉ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡና በ3ኛው ዙር የአመራር ስልጠና ላይ የሚገኙ የመንግስት አመራር አባላት በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።


 

ይህንኑ የአመራር አባላት ጉብኝት አስመልክተው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ከዕዳ ወደ ምንዳ በሚል ርዕስ ለ3ኛ ዙር በአዲስ አበባ የስልጠና ማዕከል እየሰለጠኑ የሚገኙ ከሁሉም የሃገራችን ክፍሎች የተውጣጡ የመንግስት አመራሮች አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ግዙፍ እና ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም የሁላችን ቤት በሆነችው አዲስ አበባ የሰራናቸው ስራዎች ወደ ሌሎች የሃገራችን አካባቢዎች መስፋፋት፣ ተቀናጅቶና ተናብቦ መስራትን እንደሚያጠናክሩ ገልጸውልናል በቀጣይም የህዝባችንን ኑሮ የሚያቀሉ ፕሮጀክቶችን በመለየት መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም