ቀጥታ፡

በአቶ አደም ፋራህ የተመራው የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ልዑክ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ሙዚየምን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 9/2016 (ኢዜአ) ፦ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራው የፓርቲው ከፍተኛ ልዑክ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ሙዚየምን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱም የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ታሪካዊ አመጣጥ፣ የዕድገት ጉዞ እንዲሁም ፓርቲው ለቻይና የኢኮኖሚ ዕድገት ስኬት የተጫወተውን ሚና ቡድኑ ተመልክቷል፡፡


 

በዚህም የኢትዮጵያውያንን የሥራ ባህል በማዳበር ሁሉም ዜጋ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የራሱን ሚና እንዲጫወት ማድረግ የሚያስችል ሁኔታን ልዑኩ መገንዘቡም ተጠቅሷል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ስለወደብ እንቅስቃሴ እና አጠቃላይ የማስፋፊያ ስራዎችን በተመለከተ ከቻይና ወደብ አስተዳደር ለልዑኩ ገለፃ እንደተደረገለት በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም