ታላቁ ሩጫ የከተማችንን መልካም ገፅታና አብሮነት በመገንባት በኩል ትልቅ አስተዋፅዖ እያበረከተ ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

142

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 9/2016 (ኢዜአ) ፦ ታላቁ ሩጫ የከተማችንን መልካም ገፅታና አብሮነት በመገንባት በኩል ትልቅ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ይገኛል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ውድድር በታላቅ ድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።


 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ውድድሩን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ታላቁ ሩጫ የከተማችን ተጨማሪ ድምቀት፣ የአብሮነትና የፍቅር መገለጫ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

ከንቲባዋ አክለውም ላለፉት 23 ዓመታት በድምቀት ሲከናወን የቆየው ይህ ውድድር ዘንድሮ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የከተማችን ነዋሪዎች፣ አምባሳደሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም አትሌቶች የተሳተፉበት ነው ብለዋል።


 

ታላቁ ሩጫ የከተማችንን መልካም ገፅታና አብሮነት በመገንባት በኩል ትልቅ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ይገኛል ሲሉም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም