ቀጥታ፡

የኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ትኩረት ተደርጓል 

አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2016(ኢዜአ):- የኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራትና ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን  የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ።  

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ከዘርፉ ተዋንያን ጋር እየገመገመ ነው።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በኢትዮጵያ ሥራ አጥነት ማክሮ ኢኮኖሚውን እየፈተነው ይገኛል ብለዋል። 

በኢትዮጵያ የሥራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ የሚሰለጥነውን የሰው ኃይል ከኢንዱስትሪዎች ፍላጎት ጋር  ለማጣጣም እየተሰራ ነው ብለዋል። 


 

ለዚህም የኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የተጀመረውን መሠረታዊ ለውጥ ከዳር ለማድረስ የሰው ኃይላችንን ምርታማ ማድረግ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል።

የአገር ውስጥና የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ለማቀላጠፍ ዘርፉን በቴክኖሎጂ መምራት ወሳኝ መሆኑ ታምኖበት በትኩረት እየሰራን ነው ብለዋል።

የ2016 በጀት ዓመት የሥራ ዕድል ፈጠራና ስምሪቱን በአዳዲስ እሳቤዎች መምራት የተጀመረበት መሆኑንም ገልፀዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም