ቀጥታ፡

በመጪው ፓሪስ ኦሎምፒክ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን የመለማመጃ ስታዲየም ፈቃድ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

 አዲስ አበባ ፤ህዳር 8/ 2016 (ኢዜአ):- በፓሪስ የኦሎምፒክ ውድድር  ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን የመለማመጃ ስታዲየም ፈቃድ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱ የተፈረመው በፓሪሱ አንቶኒ ክፍለከተማ ከሚገኝ ስታዲየም  ጋር ነው።

በሐምሌ ወር ለሚጀምረው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የአትሌቲክስ ቡድኑ ለሚያደርገው ልምምድ የሜዳ ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና የአንቶኒ ክፍለከተማ ከንቲባ  ከንቲባ ዣን-ኢቭ ሶናሌ ናቸው።

በፓሪሱ ኦሎምፒክ በፈረንሳይ እና በሌሎች የአውሮፓ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለቡድኑ አቀባበል ለማድረግ እና በውድድሮች ላይ በመገኘት ቡድኑን ለመደገፍ የሚያስችሉ የዝግጅት ስራዎችን ለመስራትም ከደጋፊ ተወካይች ጋር ውይይት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያውያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊኑ ኦሎምፒክ ቡድኑ አመርቂ ውጤት እንዲያመጣ እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም