ቀጥታ፡

የስራ ላይ ስልጠና ያጠናቀቁ 5ሺህ 193 ወጣቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 7/2016(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዲስትሪ ልማት ቢሮ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር "ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ መርሐግብር "ተሳታፊ 5ሺህ 193 ወጣቶችን አስመረቀ።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ከተማ አስተዳደሩ በስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች በርካቶችን ከስራ በማገናኘት ራሳቸውን እንዲችሉና ሀብት እንዲፈጥሩ ማድረጉን ገልጸዋል።

መርሐግብሩ የሰለጠነ የሰው ኃይል ዕጥረት እያለ ብዙዎች ስራ ፈላጊ የሆኑበት ሁኔታ ለማስተካከል ወጣቶችን ከኢንዱስትሪ ጋር በማገናኘት በአስተሳሰብ ተቀይረው በክህሎት በቅተው እጆቻቸውን ከስራ ማገናኘት ማስቻሉንም ተናግረዋል።


 

በሁለተኛው ዙር መርሐግብር ከ15 ሺህ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

መርሐግብሩ እንዲሳካ ሰልጣኞችን ተቀብለው በማሰልጠን ብቁ በማድረግና በመቅጠር አስተዋፅዖ ያበረከቱ ልበ-ቀና ተቋሞችን አቶ ጃንጥራር አመስግነዋል።

ወጣቶች ከተማ አስተዳደሩ በሚፈጥራቸው ዕድሎች በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም