ቀጥታ፡

ፍትሐዊ የወደብ አጠቃቀምን የተመለከተ ልዩ ሴሚናር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 7/2016(ኢዜአ)፦ፍትሐዊ የወደብ አጠቃቀምን የተመለከተ ልዩ ሴሚናር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመካሔድ ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርስቲው ያዘጋጀው ሴሚናር "ፍትሐዊ የወደብ አጠቃቀም ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና ልማት" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ነው።

በሴሚናሩ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፣ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ወደቦችን የመጠቀም ፍላጎት ከጂኦፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሕግና ዲፕሎማሲ አኳያ ጽሑፎች ቀርበው ምክክር እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም