ቀጥታ፡

የፊፋ ዋና ፀሐፊ ለሥራ ጉብኝት ድሬዳዋ ገቡ

ድሬዳዋ ፤ ህዳር 5/2016(ኢዜአ)፦ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ዋና ፀሐፊ ፋጡማ ሳሞራይ ለሥራ ጉብኝት ማምሻውን ድሬዳዋ ገቡ።

ዋና ፀሐፊዋ ማምሻውን ድሬዳዋ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ ሲገቡ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዋና ፀሐፊዋ በድሬዳዋ ቆይታቸው የሕፃናት የእግር ኳስ ፕሮጀክትና በስፖርት ዘርፍ የሚካሄዱ ተግባራትን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተለይም በድሬዳዋ ስታዲየም በ50 ሚሊዮን ብር ወጪ የመጫወቻ ሜዳውን ሰው ሰራሽ ሣር የማልበስና በስታዲየሙ የተሰሩ ሌሎች የልማት ስራዎችን እንደሚመለከቱ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም