የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 5/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር በሪሶ አመሎ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ስምምነቱን ፈርመዋል።
የተደረገው ስምምነት ሁለቱ ተቋማት በጋራና በትብብር የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያግዛቸው መሆኑን ዶክተር በሪሶ ገልጸዋል።
የድሬደዋ ነፃ የንግድ እንቅስቃሴን ለማጎልበትም ስምምነቱ የላቀ አስተዋጽኦ የሚኖረው መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ፤ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን አብራርተዋል።
በመሆኑም የተደረገው ስምምነት ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በፍጥነትና ጥራታቸው ተጠብቆ ወደ ንግድ ቀጠናው እንዲገቡ ለማድረግ የሚረዳ ነው ብለዋል።