ቀጥታ፡

8ኛው ሀገር አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራዎች ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 5/2016 (ኢዜአ) ፦8ኛው ሀገር አቀፍ የተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራዎች ውድድር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተጀመረ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት መሪ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን ንጋቱ  ኤግዚቢሽኑን ሲያስጀምሩ እንዳሉት  የፈጠራ ስራዎች ለዛሬ ውጤት ብቻ ያለሙ ሳይሆን የነገይቱን የሀገራችንን ችግር የሚፈቱ ሊሆኑ ይገባል ።

 ዛሬ አድገው የምናያቸው ሀገሮችም ለደረሱበት እድገት ዋናው ሚስጥር ሳይንስ ነው ብለዋል።

የስቲም ካንትሪ ዳይሬክተር ወይዘሮ አሰገደች ሻውል በበኩላቸው የሳይንስ ትምህርቶችን በተግባር አስደግፎ ለማስተማር  ከትምህርት ቤት እስከ ዩኒቨርስቲዎች ያሉ የፈጠራ ስራዎቸን ለማጠናከር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እንሰራለን ብለዋል።


 

በትምህርት ሚኒስቴር የሂሳብ ሳይንስና ስነ-ጥበብ ዴስክ ኃላፊ አቶ ታደሰ ተሬሳ በዚህ ሀገር አቀፍ የፈጠራ ስራዎች ውድድር 211 ችግር ፈች የፈጠራ ስራዎች እንደቀረቡ ገልጸዋል።

የተማሪዎችን ችግር ፈች የፈጠራ ስራዎች ለማሳደግ የመምህራን ብቃት ማደግ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ግንባታ ስራ ላይ  በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

 የፈጠራ ስራ ውድድር ና  ኤግዚቢሽኑም ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ  ከሚስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም