ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከፈረንሳይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከፈረንሳይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 05/ 2016 (ኢዜአ) :-የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከፈረንሳይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ።
የተመድ የትምህርት ፣የሳይንስና የባህል ድርጅት 42ኛዉ (የዩኔስኮ) አጠቃላይ ጉባኤ የኢትዮጵያ የትምህርት ልዑካን ቡድን ተሳታፊ ሆኗል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስትርና የብሔራዊ ዩኔስኮ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በፈረንሳይ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የባህል፣ ትምህርትና ዓለም አቀፍ ልማት የሥራ ኃላፊ ከሆኑት ኦልቪዬ ሪቻርድ ጋር ተወያይተዋል ።
በውይይታቸውም በፈረንሳይ እና በኢትዮጵያ መንግሥታት መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለውን ትብብር የበለጠ በሚጠናከርበት ሁኔታን አንስተዋል።
ፈረንሳይ የኢትዮጵያ መንግሥት የትምህርት ጥራትና ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ የምታደርገውን የሪፎርም ሥራዎችን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በውይይቱ ተነስቷል።
በቅርቡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድር ዩኒቨርስቲ ሆኖ እንዲደራጅ መወሰኑንና ቀጣይም ሌሎች ስምንት ዩኒቨርስቲዎችን ወደዚሁ ሂደት ለማሸጋገር የተጀመረውን እንቅስቃሴ ላይ የፈረንሳይ መንግሥት የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርግ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጥሪ አቅርበዋል።