ጃፓን ለኢትዮጵያ ለጤና አገልግሎት የሚውሉ አምቡላንሶችና የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገች - ኢዜአ አማርኛ
ጃፓን ለኢትዮጵያ ለጤና አገልግሎት የሚውሉ አምቡላንሶችና የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገች
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 4/2016 (ኢዜአ)፦የጃፓን መንግሥት ለአማራና ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከ12 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው አምቡላንሶችና የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ለሁለቱ ክልል ተወካዮች አስረክበዋል።
አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ድጋፉ በሁለቱ ክልሎች ለሚገኙ ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።
ድጋፉ በጃፓንና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን አጋርነት የሚያጠናክር መሆኑንም አንስተዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ደርጅት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ኮፊ ኮኡዋሜ በበኩላቸው፤ ድጋፉ በድርጅቱ ፕሮግራም ሥር የሚውል መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም ድጋፉ ተቋማቸው በኢትዮጵያ የሚሰራውን ሥራ ያጠናክራል ብለዋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የጃፓን መንግሥት በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ለሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አመስግነዋል።
ድጋፉ በሁለቱ ክልሎች የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው፤ በድጋፉ የጤና ተቋማትን ለማደራጀት ያስችላል ነው ያሉት። በቀጣይም የጃፓን መንግሥት በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስትር ዴኤታው ጥሪ አቅርበዋል።