ዴቪድ ካሜሩን የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ተሾሙ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2016(ኢዜአ)፦የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን የሀገሪቱ አዲስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ተሹመዋል።

በካቢኔያቸው ሹም ሽር እያደረጉ የሚገኙት የወቅቱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ያልተጠበቀ ሹመት መስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

በዚህም እንግሊዝን እ.አ.አ ከ2010 እስከ 2016 በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ዴቪድ ካሜሩንን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውን ነው ዘገባው ያመለከተው።

የ57 አመቱ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ካሜሩን ከ7 ዓመታት በፊት ከፖለቲካው መድረክ በመራቅ በቢዝነስ ስራ ላይ ተሰማርተው መቆየታቸው ተዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም