የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎችን ለማድረግ ሞሮኮ ገባ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎችን ለማድረግ ሞሮኮ ገባ
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 2/2016 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመርያ እና ሁለተኛ የምድብ ጨዋታዎችን ለማድረግ ሞሮኮ ካሳብላንካ ገብቷል።
በካሳብላንካ ኢቢስ ሆቴል ማረፊያውን ያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ ህዳር 5/2016 ከሴራሊዮን እንዲሁም ህዳር 11/2016 ከቡርኪና ፋሶ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር አልጀዲዳ ከተማ ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።
ብሔራዊ ቡድኑ 23 ተጫዋቾችን በመያዝ ለማጣሪያ ጨዋታዎቹ በአዲስ አበባ የዝግጅት ልምምዱን ሲያደርግ መቆየቱን ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።