ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሳዑዲ-አፍሪካ ጉባዔ ላይ ያደረጉት ንግግር ፋይዳው የጎላ መሆኑን የሳዑዲ ጋዜጣ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 1/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሳዑዲ-አፍሪካ ጉባዔ ላይ ያደረጉት ንግግር ፋይዳው የጎላ መሆኑን የሳዑዲ ጋዜጣ ዘግቧል።

በሳዑዲ - አፍሪካ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ንግግር አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካንና ሳዑዲ አረቢያ ታሪካዊ ግንኙነት ማንሳታቸውንና የሳዑዲ-አፍሪካ ግንኙነት ለማጠናከር በርካታ አቅሞች  እንዳሉም መግለጻቸውን ጠቅሷል።

ሳዑዲ አረቢያ በአፍሪካ ወሳኝ ዘርፎች ላይ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ያላት ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ሲሉ መግለጻቸውንም በዘገባው አስፍሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በንግግራቸው ሳዑዲ አረቢያ በአፍሪካ በታዳሽ ኢነርጂ፣ በመሰረተ ልማት፣ በግብርና፣ በጤናና በትምህርት ዘርፍ መዋለ ንዋይን ለማፈሰስ እያሳያች የለው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ የረጅም ዓመታት መልካም ግንኙነት ያላቸው አገሮች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸውንም  ጠቅሷል።

ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ይበልጥ ማሳደግ እንደምትፈልግም ማንሳታቸን በዘገባው አስፍሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግብርናው ሴክተር የኢትየጵያ ዋና የአኮኖሚ መሰረት መሆኑን ጠቅሰው የሳዑዲ ኢንቨስተሮች  በግብርናው ዘርፍ መዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሁለቱን አገራት የጋራ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ የተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት ኢትየጵያ ቁርጠኛ መሆኗን መግለጻቸውንም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም