ምልምል ፖሊሶች በስልጠናው ባገኙት ፖሊሳዊ ሙያ የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ በተጠናከረ ሁኔታ ለማስጠበቅ መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
ምልምል ፖሊሶች በስልጠናው ባገኙት ፖሊሳዊ ሙያ የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ በተጠናከረ ሁኔታ ለማስጠበቅ መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፤ ህዳር1/2016(ኢዜአ)፦ ዛሬ የተመረቁት ምልምል ፖሊሶች በስልጠናው ያገኙትን ሙያ ፖሊሳዊ ስነምግባርን በመላበስ የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ በተጠናከረ ሁኔታ ለማስጠበቅ መስራት እንደሚኖርባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው አሳሰቡ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ለ28ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ምልምል ፖሊሶች አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ በኦሮሚያ ክልል ቡልቡላ ማሰልጠኛ ተቋም መደበኛ የፖሊስ ስልጠናቸውን የወሰዱ ሲሆን ከተመረቁት ፖሊሶች ውስጥ 779 ሴቶች ናቸው።
ተመራቂዎቹ በስልጠናው ያገኙትን ሙያ ፖሊሳዊ ስነምግባርን በመጠበቅ የከተማዋን ህዝብ ሰላምና ፀጥታ በማስከበር የሚጠብቅባቸውን ሃላፊነት በብቃት እንዲወጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በመርሃ ግብሩ ላይ አሳስበዋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክርቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልካድር፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንዲሁም ሌሎች የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።