ቀጥታ፡

ኮርፖሬሽኑ የግንባታ ዘርፉን አቅም የሚያጎለብቱ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 1/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ  ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የግንባታ ዘርፉን አቅም የሚያጎለብቱ  ፕሮጀክቶች አስመረቀ።

በምርቃት  ስነ- ስርዓቱ ላይ የህዝብ  ተወካዮች  ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ  ታገሰ ጫፎ፣ የመከላከያ  ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም  በላይን ጨምሮ  ሚኒስትሮች፣  ከፍተኛ  የመንግሥት  የስራ ሃላፊዎችና  ጥሪ የተደረገላቸው  እንግዶች ተገኝተዋል ።

ኮርፖሬሽኑ  ዛሬ ለምርቃት  ካበቃቸው ፕሮጀክቶች  መካከል የግንባታ ባለሙያዎች  ልማት ኢኒስቲትዩት ፣ የግንባታ  ኢንዱስትሪዎች ግብአት ማምረቻና ማከፋፈያ እንዲሁም ቢውልዲንግ ኢንፎርሜሽን ሞዴሊንግ ይገኙበታል ።

ከዚህ ባለፈም ኮርፖሬሽኑ ያለፈባቸውን ሂደቶች የሚያስቃኙ የፎቶግራፍ  አውደ- ርዕይ ለጎብኚዎች  ክፍት አድርጓል።

ተቋሙ በአስር ዓመቱ ከያዛቸው የልማት ፕሮግራሞች ውስጥ  የግንባታ  ዘርፍ አንዱ ሲሆን ዘርፉን  በሰው ሃይልና ቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንዲሆን እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ዛሬ ለምርቃት የበቁት ፕሮጀክቶች በመስኩ የተሻለ ስራ ለማከናወን  ተጨማሪ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም