ቀጥታ፡

የኢትዮ -ጅቡቲ ትራንስፖርት ኮሪደር ፕሮጀክት አካል የሆነው የአዳማ - አዋሽ ምዕራፍ አንድ የፍጥነት መንገድ የአስፋልት የማንጠፍ ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2016 (ኢዜአ)፡- የኢትዮ -ጅቡቲ ትራንስፖርት ኮሪደር ፕሮጀክት አካል የሆነው የአዳማ - አዋሽ ምዕራፍ አንድ የፍጥነት መንገድ የአስፋልት የማንጠፍ ሥራ ተጀመረ። 

የአዳማ-አዋሽ ምዕራፍ አንድ አዳማ ኪሎ ሜትር 60 የፍጥነት መንገድ 61 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር እርዝማኔ ያለው ሲሆን ፣ ግንባታው ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና ከመንግሥት በተገኘ በ 6 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ ነው። 

የፍጥነት መንገዱን አገናኝ መንገዶችን ፣ ማሳለጫ መንገዶችን ፣ የክፍያ ጣቢያዎችን ፣ የመኪና እና የእግረኛ መሸጋገሪያ ድልድዮችን ያካተተ መሆኑን  የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር መረጃ ያመለክታል።

መንገዱ ትልልቅ የድልድይ ግንባታ ፣ ማሳለጫዎችና ማቋረጫዎች ፣ የአቃፊ ግንብ ፣ የመንገድ ዳር የትራፊክ ምልክቶች ፣ የደህንነት ካሜራዎችን ፣ ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን ያካተተ መሆኑም ተገልጿል፡፡ 

የፍጥነት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት  ሲጠናቀቅ የመስመሩን የትራፊክ ፍሰት ለማቀላጠፍና የተሽከርካሪዎች የጉዞ ጊዜና ዋጋ በመቀነስ አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም