ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጀመሪያው የሳዑዲ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጀመሪያው የሳዑዲ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ገቡ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 30/2016 (ኢዜአ) ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጀመሪያው የሳዑዲ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በመጀመሪያው የሳዑዲ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል::