አቶ አህመድ ሽዴ ከሳዑዲ የገንዘብ ሚኒስትር መሃመድ አል ጅዳን ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ አህመድ ሽዴ ከሳዑዲ የገንዘብ ሚኒስትር መሃመድ አል ጅዳን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30/2016 (ኢዜአ)፦ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከሳዑዲ ዓረቢያ የገንዘብ ሚኒስትር መሃመድ አል ጅዳን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው የኢኮኖሚ ሪፎርም ልማት እና እዳ ሽግሽግ ላይም ምክክር አድርገዋል።
የሳዑዲ ዓረቢያ ፋይናንስ ሚኒስትር መሃመድ አል ጅዳን መንግስታቸው በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ለሚገኙ የልማት እንቅስቃሴዎች በቀጣይነት ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውንም በሳዑዲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ውይይቱ በሪያድ እየተካሄደ ከሚገኘው የሳዑዲ ዓረቢያ- አፍሪካ ኢኮኖሚ ኮንፍረንስ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡