ቀጥታ፡

አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተጠሪ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 29/2016 (ኢዜአ):-  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ኤርትራ ፣ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ተጠሪ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

እየተተገበሩ ባሉ የለውጥ ሥራዎች፣ በፕሮጀክት ፋይናንስ እና በሌሎች ትብብር በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም