በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር የተመራ ልዑካን ቡድን የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድርን እየጎበኘ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር የተመራ ልዑካን ቡድን የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድርን እየጎበኘ ነው
ዲላ ፤ ጥቅምት 29/2016 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ የተመራ የልዑካን ቡድን በዩኔስኮ የተመዘገበውን የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እየጎበኘ ነው ።
በጉብኝቱም የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌውን ጨምሮ የስነ-ቅርስ ጥናት ተመራማሪዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ልዑካን ቡድኑ በቆይታው የቱቲቲ እና ቱቲፈላ መካነ ቅርስን ጨምሮ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር ገፅታዎችን ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል።
በኢትዮጵያ በፈረንሳይ የጥናትና ምርምር ማዕከል የጌዴኦ ታሪካዊ የትክል ድንጋዮች መካነ ቅርስ ምርምርና ጥናት እየተካሄደ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።