“የሀገር ግንባታ መሠረታውያን” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
“የሀገር ግንባታ መሠረታውያን” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 29/2016 (ኢዜአ)፦ “የሀገር ግንባታ መሠረታውያን” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የፓናል ውይይቱን የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው።
በመድረኩ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የሀገር ግንባታ መሠረታውያን መነሻ ጉዳዮች፣ ሀገራዊ ማንነትና እሴቶች ለሀገር ግንባታ እና ሀገራዊ ጥቅሞች ለሀገር ግንባታ በሚል የተዘጋጁ ጽሁፎች በምሁራን ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።