የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛውን የቦይንግ የጭነት አውሮፕላን አስገባ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛውን የቦይንግ የጭነት አውሮፕላን አስገባ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛውን የቦይንግ (Boeing 777-200LR) የጭነት አውሮፕላን ማስገባቱን አስታወቀ።
አውሮፕላኑ ዘመናዊ ባለሁለት ሞተር መሆኑንና ከመቶ ቶን በላይ ጭነት የመሸከም አቅም እንዳለው ተጠቅሷል።
እስከ አሁን ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች የምዝገባ ኮድ በA የሚጀምር የነበረ ሲሆን የዚህ አዲስ አውሮፕላን ምዝገባ ኮድ ግን በB በመጀመር ET-BAA የሚል ስያሜን በመያዝ አዲስ የአውሮፕላን ምዝገባ ምእራፍ መክፈቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመላክታል።