የ"ታላቁ የአፍሪካ አረንጓዴ ግንብ ኢንሼቲቭ" አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደረገ ስብስባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 28/2016 (ኢዜአ)፦ የ"ታላቁ የአፍሪካ አረንጓዴ ግንብ ኢንሼቲቭ" አፈጻጸም የሚገመግም ስብስባ በአፍሪካ ሕብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

 “ታላቁ የአፍሪካ አረንጓዴ ግንብ ኢንሼቲቭ" በረሀማነትን ለመከላከል 8 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ደን በሳሄል ቀጣና ለመትከል ያለመ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። 

በስብስባው የኢትዮጵያ ደን ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሞቱማ ቶሌራ፣የአፍሪካ ሕብረት ግብርና፣ገጠር ልማት፣ብሉ ኢኮኖሚና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽን ተወካዮች፣የደን  ልማት፣አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ላይ የሚሰሩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።   

  ከአፍሪካ ሕብረት ዋነኛ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ኢንሸቲቭ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር  በ2007 የተጀመረ ሲሆን፤ ዓላማውም የሰሃራ በረሃ መስፋፋትን ለመከላከልና በቀጣናው የሚገኙ አገራትን ኢኮኖሚ ማሻሻል እንደሆነ ተገልጿል። 


 

ለኢኒሼቲቩ ተፈጻሚነት የልማት አጋሮች፣ዓለም አቀፍ ተቋማትና የተለያዩ አገራት የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያም ኢኒሼቲቩን ከመሰረቱና ስምምነቱን ከፈረሙ የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ስትሆን፤ በአማራ፣ትግራይና አፋር ክልሎች በሚገኙ 58 ወረዳዎች እየተገበረችው ትገኛለች፡፡

በወረዳዎቹ እየተከናወነ ያለው ስራ 13 ሄክታር የተራቆተ መሬት በደን መልሶ ለመሸፈን የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም