የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ የኢትዮጵያ ድርጅቶች የተሳተፉበት ኤክስፖ በቻይና እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 28/2016(ኢዜአ)፦ በሻንሀይ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የቻይና ኢንተርናሽናል ኢምፖርት ኤክስፖርት ኤክስፓ ላይ የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን በማስተዋወቅ እየተሳተፉ ይገኛሉ።


 

ኤክስፖው ከተለያዩ ከተሞች ከመጡ ሰዎች በተጨማሪ በተለያዩ የቻይና የንግድ ተጠሪ ድርጅቶችና በማህበራት ሀላፊዎች መጎብኘቱም ተጠቅሷል።

ከኤክስፖው ጎን ለጎን በሚካሄዱ የማስተዋወቂያ መድረኮች ላይ የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ዕድሎች፣ የወጪ ምርቶች እና የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅ መቻሉን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም