ቀጥታ፡

ከአንድ መቶ በላይ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት 'የኛ ምርት' የተሰኘ ኤግዚቢሽንና ባዛር በመጪው ታህሳስ ይካሄዳል 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2016(ኢዜአ)፦ከአንድ መቶ በላይ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት 'የኛ ምርት' የተሰኘ አገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር በመጪው ታህሳስ ይካሄዳል። 

ኤግዚቢሽንና ባዛሩ “ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት“  በሚል መሪ ቃል ከታህሳስ 3 እስከ 7 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች ሁነቱን ይጎበኙታል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤግዚቢሽንና ባዛሩን አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የተቋሙ  ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አለባቸው ንጉሴ  በኢንተርፕራይዞች የሚመረቱ ምርቶች እንዲተዋወቁና ለገበያ እንዲቀርቡ ከማድረግ አኳያ ያለው ፋይዳ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችንና ተግዳሮቶችን በሚመለከት የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል።

በኤግዚቢሽን እና ባዛሩ ላይ ከ100 በላይ በተለያዩ ዘርፎች  የተሰማሩ አምራች ኢንተርፕራይዞች እንደሚሳተፉ ተጠቁሟል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም