ከ250 አመታት በኋላ ለንባብ የበቁት የፍቅር ደብዳቤዎች - ኢዜአ አማርኛ
ከ250 አመታት በኋላ ለንባብ የበቁት የፍቅር ደብዳቤዎች
ለወዳጅ ዘመድኦ ሀሳበዎ በአስቸኳይ ይደርስ ዘንድ የላኩት መልዕክት በወቅቱ ሳይደርስ እና ሀሳብዎት ሳይተላለፍ ለዓመታት ቢቆይ ምን ይሰማወታል?
ከወደእንግሊዝ ከ250 አመታት በኋላ ለንባብ የበቁት የፍቅር ደብዳቤዎች ታሪክ መረጃ ግን አጃይብ ያሰኘ ዜና ሆኗል።
ታሪኩ እንዲህ ነው በሰባት አመታቱ እንግሊዝና ፈረንሳይ ጦርነት ወቅት የተጻፉት 104 ደብዳቤዎች ለተጻፈላችው ሰዎች ሳይደርሱ በእንገሊዟ ኪው የተሰኘች እጽዋት ቤተ-መዘክር ተከማችተዋል።
እኒሁ ደብዳቤዎች ለፍቅረኛሞች የተጻፉ ናቸው በእንግሊዝና ፈረንሳይ መካከል ለሰባት አመታት በተካሄደው ጦርነት 181 ባህረኞችን ከያዘችው የፈረንሳይ የባህር መርከ ከተጻፉት የፍቅር ደብዳቤዎች ሩቦቹ እንኳን ለተላከላቸው አካላት አልደረሱም።
ከእነዚህ ደብዳቤዎች መካከልም የፈረንሳዩ ባህር ሀይል በ1757 ዓም አካባቢ በጦርነት ወቅት ለፍቅረኛው የጻፈው ደብዳቤው ይገኝበታል። ደብዳቤው የፍቅረኛውን ውብት በተዋቡ ቃላት የሚገልጽና ያለበትን ሁኔታ የሚያትት መሆኑን የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሪናውድ ሞሬክስ ለጥናት መረጃዎች ሲያሰባስቡ ያገኙትን አስደናቂ ደብዳቤዎች ለህትመት ሲያበቁ ገልጸዋል።
ዳብዳቤውን ለማድረስ የፈረንሳይ ፖስታ አስተዳደር በተለያዩ ወደቦች ቢያዘዋውረውም ሳይሳካ መቅረቱን ያወሳው የቢቢሲ ዘገባ፤ ከዚያም ወደ እንግሊዝ በመመለስ በኪው ቤተ መዘክር እንዲቀመጥ ተደርገዋል።
“ዳብዳቤውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብኩት በጥልቅ ስሜት ውስጥ ሆኜ ነው ምንም እንኳ ወታደራዊ ምስጥር ባይኖረውም” ይላሉ ፕሮፌሰሩ ሪናዋድ ሞሪዩክስ።
ከደብዳቤዎቹ መካከል ሌላዋ የመርከቧ ረዳት ካፒቴን ዶቦስክ ለባለቤቷ ሊዊሰ ቻምበርሊን የጻፈችው ይገኝበታል። ባለቤቷ በእንግሊዞች መያዙን ያላወቀቺው ሊዊስ ቻምበርሊን “ውድ ባለቤቴ የፍቅሬን ጥልቀት ለመግለጽ ሌሊቱን ሁሉ አሳልፌያለሁ” ስትል ገልጻለች።
ደብዳቤውን በጻፈችም በአመቱ በሰሜናዊቷ ፈረንሳይ አርፋለች። ባለቤቷ ቻምበርሊንም ወደ ፈረንሳይ በ1761 ተመልሶ ዳግም ሌላ ህይዎት መመስረቱን በመረጃው ተጠቅሷል።
ሌላው በደብዳቤ ታሪክነት የተመዘገበው አና ለባለቤቷ ሰረፍ ጃን “እንዳላጣህ እፈራለሁ፤ ሁሌም አስብሀለሁ’’ ስትል የከተበችው ይገኝበታል።
እነዚህ ደብዳቤዎች የፈረንሳይ ባቻ ሳይሆን የሁሉንም ሰው የ18ኛው ክፍለ ዘመን ታሪክን እና ስሜትን እንዲሁም የወቅቱን የመረጃ መለዋወጫ ሂደትን እንደሚያስቃኝ ተመራመሪው ፐሮፌሰር ሞሪዩክስ ጠቁመዋል።
እንደዛሬው የማህበራዊ ድረገጾች ዙምና ዋትስ አፕን የመሳሰሉ የሀሳብን መለዋወጫዎች ሳይኖሩ ሰዎች በህይወታቸው የሚያሳልፋቸው ፈተናዎችን ለወዳጆቻቸው ለማካፈል ምን ያህለ አስቸጋሪ አንደነበረ መገንዘብ እንደሚቻል ተመራማሪው አስረግጠዋል።