በሱዳን በጦርነት ቀጣና ውስጥ ያሉ ዜጎችን የማስወጣት ሥራ እየተከናወነ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በሱዳን በጦርነት ቀጣና ውስጥ ያሉ ዜጎችን የማስወጣት ሥራ እየተከናወነ ነው
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 26/2016 (ኢዜአ)፡-በሱዳን የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገሪቱ ለመውጣት ያልቻሉትን እና ጦርነቱ በሚካሄድባቸው ቀጣና ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መንግስት የማስወጣት ሥራ እያከናወነ ነው።
ይህንኑ የማስወጣት ሥራ እያስተባበረ ያለው በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመው ግብረኃይል ዓርብ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ተመላሾችን ያሳፈሩ አራት አውቶቡሶችን ከካርቱም በመተማ በኩል ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ አድርጓል።
የተቋቋመው ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተመላሾች ወደ የቤተሰቦቻቸው እስኪደርሱ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከአሁን በፊት ቁጥራቸው ከ34 ሺ 700 በላይ ኢትዮጵያውያን ከጦርነት ቀጣና ወጥተው ወደ ሀገራቸው መግባታቸው ይታወሳል።