አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከጃፓን የኢንዱስትሪና የቤት ግንባታ ዓለም አቀፍ ማህበር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከጃፓን የኢንዱስትሪና የቤት ግንባታ ዓለም አቀፍ ማህበር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 26/2016 (ኢዜአ) ፦ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከጃፓን የኢንዱስትሪና የቤት ግንባታ ዓለም አቀፍ ማህበር (JIBH) ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ኩኒሂሮ ሃሺሞቶ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይታቸውም በኢትዮጵያ እያደገ ለመጣው የቤት ፍላጎት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት የጃፓን የዘርፉ ቴክኖሎጂዎችንና ልምድ ማሸጋገር ስለሚቻልበት ሁኔታ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
በቀጣይም ከኢትዮጵያና ከጃፓን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ተከታታይ ውይይትና ጉብኝት ለማካሄድ መስማማታቸውን በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡