ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ የተቋቋመውን የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል መረቁ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ የተቋቋመውን የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል መረቁ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25/2016 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ3 ዓመት በፊት እንዲቋቋም አቅጣጫ ባስቀመጡት መሰረት አዲስ የተቋቋመውን የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል ዛሬ ረፋድ ላይ መርቀዋል።
ማዕከሉ በተፈጥሮ እና በአደጋ ምክንያት የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በሀገር ውስጥ አጋዥ ቁሶችን ለማምረት እና ለማቅረብ የተቋቋመ ማዕከል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ማዕከል አጋዥ ቴክኖሎጂዎችን ለማምረት፣ ለማደስ እና ለማቅረብ የተቋቋመ ሲሆን ተደራሽ፣ ጥራት ያለው እና ደንበኛ ተኮር የሰው ሰራሽ እና የአካል ድጋፎች አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።