ቀጥታ፡

​​​​​​አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን በዋና አሰልጣኝነት ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23/2016 (ኢዜአ)፡- አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን በአንድ ዓመት ውል መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ከዚህ ቀደም ብሔራዊ ቡድኑን ማሰልጠናቸው የሚታወስ ነው።

ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም ላለፉት ጥቂት ወራት ብሔራዊ ቡድኑን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ሲመሩ መቆየታቸው ይታወቃል።

አሰልጣኙ ኃላፊነቱን የተረከቡት የኢትዮጵያ መድን ክለብ ከማሰልጠን ጎን ለጎን መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም