አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ከህንድ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ አማካሪ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ከህንድ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ አማካሪ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 23/2016 (ኢዜአ) ፡- በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ከህንድ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ አማካሪ እና የአፍሪካ ጉዳዮች የጋራ ጸሀፊ ፕሪያ ናይር ጋር ተወያዩ።
ውይይታቸውም ከኖቬምበር 6 እስከ 7/2023 በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ዕቅድ በተያዘው የኢትዮጵያ እና ህንድ የንግድ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ያተኮረ መሆኑን በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
በተጨማሪም አሁን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል የሁለትዮሽ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብር እንዲሁም ያላቸውን ታሪካዊ የወዳጅነት እና የትብብር ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እአአ በ1997 የንግድ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።