ቀጥታ፡

በዶክተር ግርማ አመንቴ የተመራ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዑክ በጅቡቲ የወደብና ተርሚናል እንቅስቃሴን ጎበኘ 

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 22/2016 (ኢዜአ)፡-  በግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ የተመራ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዑክ  በጅቡቲ የዶራሌ ሁለገብ ወደብና የዶራሌ ኮንቴነር ተርሚናልን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝቷል። 

በጉብኝቱ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሶፊያ ካሣ፣ የጅቡቲ የመሰረተ ልማትና ኢኩይፕመንት ሚኒስትር ሀሰን ሁመድ ኢብራሂም፣ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር በሪሶ አመሎ፣ የጅቡቲ ወደብና ነፃ የንግድ ቀጣና ባለስልጣን ሊቀመንበር አቡበከር ዑመር ሀዲ ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።


 

በጉብኝቱም የዶራሌ ሁለገብ ወደብና የዶራሌ ኮንቴነር ተርሚናል የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን ለማሻሻል እየተደረጉ በሚገኙ ጥረቶች፣ በሚያጋጥሙ ችግሮችና መወሰድ በሚገባቸው የመፍትሔ ሃሳቦች ላይ ገለፃ ተደርጓል።

በግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ የተመራ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዑካን ቡድን የ2016/17 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ ሂደትን ለመመልከት ትናንት ምሽት ጅቡቲ መግባቱ የሚታወስ ነው።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም