የኢትዮጵያ ታምርት ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ታምርት ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 22/2016 (ኢዜአ) ፡- የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የክልልና ከተማ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሮችና ምክትል ከንቲባዎች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር የዘርፉ አመራሮች፣ የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመድረኩ መታደማቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡